መግለጫ – የመብት ጥያቄ በግድያና በማሸበር አይቆምም

[የኢትዮጵያውያን ካናዳውያንሙስሊሞች ማህበር በቶሮንቶ] የኢትዮጵያ መንግስት የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊና ሕጋዊ የመብት ጥያቄ በግድያ በማሸበርና በማዋከብ አቅጣጫ ለማስቀየር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለአገር መርጋጋት የማይበጅና የሙስሊሙንም ትግል የማይገድብ መሆኑን እንዲገነዘበው እንፈልጋለን።

ሕዝበ ሙስሊሙ፡ ለዲኑ፤ ለእምነቱና ለሃይማኖቱ ለሚያደርገው ሰላምዊ ትግል ካአሁን በህዋላ ወደኋላ እንደማይል በተለያየ ወቅት ለመንግስት ገልጿል። ሆኖም መንግስት ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ፤ ስምቶ እንዳልሰማ በመሆን፤ ሰላምዊውን ሕዝብ፤ አሽባሪና አክራሪ ብሎ በመስየም፤ ለዘመኑ አምባገነኖች ያልጥቀመን የትግል ስልት በመጥቀም፤ በጠመንጃና በጥይት እንዲሁም በወታደር ጋጋት፤ በመግደልና በማሰር፤ እንዲሁም በዛቻና በማሸበር፤ ኣምበረክካቸዋለሁ እያል በምከር ቤቱ ውስጥ ሲዝት ከሰነበት በሁዋላ፤ በትናንትናው እለት በደቡብ ወሎ ዞን፤ በቃሉ ወረዳ፤ በደጋንና ገርባ አካባቢውች፤ የፍጅት ዘመቻውን ጀምሯል። ኢናሊላሂ ወኢና ሊላሂ ራጇኡን። አራት ወንድሞቻችን ሸሂድ ሲሆኑ ፤ ከስምንት በላይ ወንድሞች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በየሆስፒታሉ፤ ይገኛሉ። አሁንም የፌደራል ፖሊሶች አክባቢውን ከበው የተቀመጡ ሲሆን የበለጠ ጉዳት ለማድረስ አኮብኩበው እየጠበቁ ነው። Read the full statement [pdf].